በማኅበረሰብ-ተኮርማገገሚያውስጥያሉአጋሮች
የጎንደርእናየኩዊንስዩኒቨርሲቲካናዳበሚገኘውዓለማቀፋዊየተራድኦድርጅትማስተርካርድፋውንዴሽንድጋፍአማካኝነትለሚቀጥሉትአስርዓመታትበአካልጉዳተኛወጣቶችንተጠቃሚየሚያደርግከፍተኛትምህርትንለማስፋፋት፤አዳዲስየሙያላይህክናፕሮግሞችንለማዘጋጀትእናየማህበረሰብ-ተኮርማገገሚያምርምርበጋራለመስራትተስማምተዉስራዉተጀምሯል።
ስለ ብቁነት መስፈርቶች ተጨማሪ ይወቁ [ስለ ነጻ ትምህርት ፕሮግራም ብቁነት ማገናኛ ገጽ]
ስለዚህ ፕሮጀክት
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሃገራችን በቀዳሚነት የጤና ሙያተኞችን ለማፍራት የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ኮሌጅና ማሰልጠኛ ማዕከል በሚል ስያሜ በ1947 ዓ.ም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ተመሰረተ። በሀገራችን የጤና ሙያተኞችን ለማሰልጠን በቀዳሚነት የተቋቋመው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአመሰራረቱ ጀምሮ በሂደት በተለያዩ ስያሜዎች በእድገት ጎዳና እየተጓዘ ዛሬ በሀገራችን ከሚገኙት ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ መሰለፍ የቻለ፤ በርካታ ታዋቂ ምሁራንን ለሀገር በማበርከት አኩሪ ታሪከዊ ረጅም ጉዞ የተጓዘና በመማር ማስተማሩ፤ በምርምሩና በማህበረስብ አገልግሎቱ ውጤታማ ተግባር ያከናወነ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለሀገር ዕድገትና ለህዝቦች ኑሮ መሻሻል ፋይዳ ባላቸው የትምህርት መስኮች በአንደኛ፣ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ትምህርት ይሰጣል፤ የህብረተሰብ ችግር ፈቺ ምርምር ያካሂዳል፡፡ በአሁኑ ሰአት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማስተርካርድ ፋውንዴሽን ድጋፍ ለ450 ወጣቶች ከፍተኛ ጥራት ያለው የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ይሰጣል። እንዲሁም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራን በኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና እና የምርምር እድሎችን ያመቻቻል።