ከአጋር አካላትና ባለድርሻዎች ጋር አስተዳደራዊ ስብሰባ ተደረገ ህዳር 24፡ 2010 ዓ.ም

 

ህዳር 21 2010 ዓ.ም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ . . አር ቢሮ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ቡድን የግለ-ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡ መድረኩ ከተወሰኑ ወራት በፊት የፀደቀዉን የማስተር ካርድ ስኮላርስ ፕሮግራም ግብ ከፍ እንዲልና እስካሁን የተከናወኑ ስራዎችን መገምገም ያስቻለ ነዉ፡፡ የማሰተርካርድ ፋዉንዴሽን፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ካናዳ የሚገኘዉ የኩዊንስ ዩኒቨርሰቲ በዚህ ዓመት መስከረም 10 ላይ ታሪካዊዉን ስምምነት ፈርመዋል፡፡

በአፍሪካ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነዉ ይህ ፕሮግራም ትልቅ አቅም ላላቸዉ ወጣት የአካል ጉዳተኞች ትኩረት ይሰጣል፡፡ ፕሮግራሙ እንደፀደቀ 20 ተማሪዎች በማሰተር ካርድ ስኮላርስ ፕሮግራም በማለፍ በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሆነዉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቅበላ ተደርጎላቸዋል፡፡

 

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ታዳሚዉን እንኳን ደህና መጣቹህ በማለት የዩኒቨርሲቲዉን ማህበረሰብ ለትጉህና ብርቱ ስራቸዉ አመስግነዋል፡፡  ምክትል ፕረዝዳንቱም ለጎንደር ዩኒቨርሲቲና ለተለያዩ የዩኒቨርሲቲዉ አካላት የተሰጡ ሀላፊነቶቸንም በማንፀባረቅ “ምንም አይነት እንቅፋቶች ቢኖሩም ተምረንበቸዉ እራሳችን በመሻሻል የህንን ልምድ ለተማሪዎቻችን ከሌላዉ የተለየ ልናደርግላችዉ ይገባል” ብለዋል፡፡

በጅማሬዉ 27 እጩዎች ለቃለ-መጠይቅ የቀረቡ ሲሆን ከነዚህም 16 ሴቶችና 11 ወንዶች ናቸዉ፡፡ የዚህ ሪፖርትም ለፕሮግራም ቢሮዉ ቀርቦ ከጸፀደቀ በኋላ ለማጠናቀቅ ወደ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳነት ቢሮ ተልኳል፡፡

. . አር ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሰለሞንም ፕሮግራሙ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ እና የተማሪዎቹ የምልመላ ሂደት ምን እንደሚመስል አጭር ገለፃ አድርገዋል፡፡ የአካል ጉዳት እጩዎችን ቃለ-መጠይቅ ለማረግም የፕሮገራም ማኔጀሩና የፐሮግራሙ ምዘናና ግምገማ ባለሞያ በየእያንዳንዳቸዉ ቤት ተገኝተዉ ማከናዎናቸዉን ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡ ይህ ተግባር ሁለት ቁልፍ ነገሮችን አረጋግጧል፡፡ አንደኛዉ የተማሪዎቹን የማመልከቻ ፎርም እና ደጋፊ ማስረጃዎችን ለማረጋገጥ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የፊት ለፊት ቃለ-መጠይቅ ለማድረግ አሰችሏል፡፡

መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች ከማመልከቻ ጊዜ ገደቡ በፊት እንዲያመለክቱ መረጃዉን ቀድመዉ ማግኝት አለመቻላቸዉ፣ በኮሚቴ ዉስጥ የተመደቡ ተቋማት ለኮሚቴ ስራ አለገኘታቸዉ፣ ያልተሟሉ ማመልከቻወች እና የዩኒቨርሲቲዉ የትምህርት ካላንደር መለወጥ ያጋጠሙ ችግሮች በሚል መድረኩ ላይ ተነስተዋል፡፡ ሆኖም እንደነዚህ አይነት ችግሮች ተቀርፈዉ ለወደፊት ተመሪዎች የልህቀት እድገት እንደሚያረጋግጡ ግልፅ ተደርጓል፡፡

የማስተርካርድ ፋዉንዴሽን እንደ አዉሮፓዊያን አቆጣጠር በ 2006 ተመስርቶ የትምህርት፣ የገንዘብ ማዕቀፍ እና የኑሮ መሠረትን ለማሻሻል እየሰራ ይገኛል፡፡ በአፍሪካ ተቀዳሚ አላማዉም የለዉጥ መሪዎችን መፍጠር ነዉ፡፡ ይህንን አላማ ለማሳካትም በአፍሪካ ቀንድ በቀጣዮቹ አስርት ዓመታት 450 የሚሆኑ የአካል ጉዳት ያለባቸዉ ተማሪዎች የህይወት ዘመን እድል ይሰጣል፡፡