የባለ ድርሻ አካላት ማነቃቂያ ስብሰባ ታህሳስ 3፣ 2010 በአዲስ አበባ ተካሄደ

በጎንደር ዩኒቨርቲና በኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ የማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ስኮላርስ ፕሮግራም የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ፕሮግራምን ለመጀመር የባለ ድርሻ አካላት ማነቃቂያ ስብሰባ ታህሳስ 3፣ 2010 በአዲስ አበባ አካሄደ፡፡

ስብሰባዉ የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ፕሮግራምን በመክፍት ተማሪዎችን ተቀብሎ በቅድመ መከላከያና ማዳኛ ዘዴዎች እና የተለያዩ አይነት የአካል ጉዳት ያለባቸዉን ሰዎች ሁሉን አቀፍ የተሃድሶ አገልግሎት በመስጠት የኑሮ ደረጃቻዉን እና ምርታማነታቸዉን ለማሻሻል የጎንደር ዩኒቨርሲቲን እቅድ ለባለ ድርሻ አካሎች ለማሳወቅ ያሰበ ነዉ፡፡ ይህ ፕግራምም በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ በአይነቱ የመጀመሪያዉ ይሆናል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካል ጉዳት ጥናቶችና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት አበበ  “በዚህ ልዩ ወቅት ሁላችንም ጥራት ያለዉ የከፍተኛ ትምህርት እድልን በመስጠት ክህሎት ኖሯቸዉ ግን ዉስንነት ያለባቸዉ ወጣቶችን ችግር መፍታት ተገቢ ነዉ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “የአካል ጉዳተኞች አሁንም ድረስ በማህበረሰባችን እንደ ተሰወሩና ችላ እንደተባሉ ነዉ፡፡ የአካል ጉዳተኝነት ጉዳይ ብዙ ገፅታ ያለዉ ሲሆን ከአካል ጉዳተኞች ባሻገር ሌላዉን የማህበረሰብ ክፍል የሚነካ ነዉ፡፡” በማለት በንግግራቸዉ አፅንኦት አድርገዋል፡፡

በአለም ባንክና በአለም የጤና ድርጅት እንደ አዉሮፓዊያን አቆጣጠር 2011 ሪፖርት መሰረት እሰከ 15 ሚሊዮን የሚጠጉ የአካል ጉዳተኛ አትዮጵያዊያን አሉ፡፡ የአካል ጉዳተኛነት አደጋዎች፣ ድንጋጤዎች፣ የዘር ወይም የበሽታዎች እና የሌሎች ብዙ መንስዔዎች ዉጤት ሊሆን ይችላል፡፡ አካል ጉዳተኞች በየእለቱ በሚያደርጉት የማህበራዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ተሳትፎዎች ሙከራ አካል ጉዳተኛ ካልሆነዉ የማህበረሰብ ክፍል ባለዉ የተዛባ መረዳትና የግንዛቤ እጥረት ምክኒያት  እክሎች ይገጥሟቸዋል፡፡

ካናዳ የሚገኘዉ ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ የማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ፕሮጀክት ተባባሪ ዳይሬክተር  ዶ/ር ሄዘር አደርሴይ በበኩላቸዉ ልዩ የሆነዉ የኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጋርነት ጥራት ያለዉ ሁሉን አቀፍ ትምህርትን ለአካል ጉዳተኞች በመስጠት፣ ተቋማዊ አቅምን በመገንባት እና የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ፕሮግራምን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመክፈት ያግዛል ብለዋል፡፡ “የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) በኢትዮጵያ የታወቀ የጤና ሞያ እንዲሆን ራዕይ ሰንቋል፡፡ ይህ አላማ ለኢትዮጵያ አስፈላጊዉን የተሀድሶ አገልግሎቶች የሚያመጣ ነዉ፡፡ ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲም  ይህንን አላማ ለማሳካት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር መሰራት በመቻሉ ክብር ይሰማናል” ብለዋል፡፡

ዶ/ር አደርሴይ እንዳሉት የማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ስኮላርስ ፕሮግራም በህዳር ወር 2016 ሲጀመር ክህሎት ኖሯቸዉ ግን ዉስንነት ያለባቸዉን የአካል ጉዳተኛ ወጣቶች እና በኢኮኖሚይ እድገት፣ በልማት፣ በማህበራዊ ለዉጥና በምስራቅ አፍሪካ አዉንታዊ ለዉጥን ማምጣት ለሚችሉ ሴቶች ጥራት ያለዉ ሁሉን አቀፍ የከፍተኛ ትምህርትን ማድረስ አልሞ ነዉ፡፡

ካናዳ የሚገኘዉ ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ የማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ፕሮጀክት ማኔጀር እና የተመዘገቡ የኦከፔሽናል ቴራፒስት (የሞያ ሀኪም) የሆኑት አኑሽካ ጆሴፍ በበኩላቸዉ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም በአለም የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ፋዉንዴሽን እዉቅና እነዲያገኝ እናመለክታለን ብለዋል፡፡ ፕሮግራሙ በቅድመ ምረቃ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሩ በፊት የዩኒቨርሲቲዉ ምምህራን በኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ ማስተርሳቸዉን ይሰለጥናሉ፡፡ ስልጠናዉን የወሰዱ መምህራን ከኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር በጋራ በመሆን የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ስርዓተ-ትምህርት ቀርፀዉ አስፈላጊዉን የፈቃድ ሂደት በመጨረስ በክልሉ ካሉ ትምህርት ቤቶች ጋር በአጋርነት የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና)በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይከፍታሉ፡፡

የኦከፔሽናል ቴራፒስትስ (የሞያ ሀኪሞች) በመንግስት፣ በግል እና በበጎ አድራጎት ተቋማት ዉስጥ እንደሚሰሩ እና ስልጠናቸዉም የአካል ጉዳተኞችን የህክምና እና የአካል ዉስንነት ወይም ጉዳት ብቻ ሳይሆን ደህንነታቸዉ፣ ጤናቸዉና አጠቃላይ ተግባራቸዉ ላይ ተፅዕኖ ስለሚያደርጉ ስነ-ልቦናዊ ጉዳዮች ለመረዳት ብቁ የሚያደርግ ነዉ በማለት አብራርታለች፡፡

እንደ የአለም ኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ፋዉንዴሽን (2012)ገለፃ መሰረት ኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ማለት  ደንበኛን ያማከለ በሞያ ጤናንና ደህንነትን የሚያራምድ የጤና ሙያ ሲሆን ተቀዳሚ ግቡም ሰዎች በየዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል ነዉ፡፡ ይህንን ዉጤት ለማምጣትም የኦከፔሽናል ቴራፒስትስ (የሞያ ሀኪሞች) ከህዝብና ማህበረሰቦች ጋር በመስራት ሰዎች የሚፈልጉትን፣ የሚያስፈልጋቸዉን ወይም እንዲሰሩ የሚጠበቅባቸዉን ለማሰቻል ሞያቸዉን  ወይም የስራ አካባቢያቸዉን በማስተካከል በሞያቸዉ ያላቸዉን ተሳትፎ ለማሻሻል በመደገፍ ነዉ፡፡ የኦከፔሽናል ቴራፒስትስ (የሞያ ሀኪሞች) በህክምና፣ በማህበረሰብ ባህሪይ፣ በስነ-ልቦና፣ በማህበራዊ ስነ-ልቦና እና በሙያ ሳይንስ ሰፋ ያለ ትምህርት ሲኖራቸዉ ይህም ከሰዎች፣ ከግለሰቦች፣ ከቡድኖች ወይም ከማህበረሰቡ ጋር ተባብረዉ ለመስራት የሚያስችል አመለካከት፣ ክህሎት እና እዉቀትን ያስጨብጣቸዋ፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ነቢዩ መስፍን በሀገር አቀፍ ማነቃቂያ ስብሰባዉ ባቀረቡት ገለፃ ወቅት አሁን በኢትዮጵያ ስላለዉ የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) አገልግሎትና ስልጠና ተናግረዋል፡፡ በንግግራቸዉም በሀገሪቱ ያለዉን የአካል ጉዳት መጠን በማሰብ የፕሮግራሙን መከፈት ጠቀሜታ ለባለ ድርሻ አካላት ዘርዝረዋል፡፡ በገለፃዉም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ እና ከማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ጋር በአጋርነት በአገር አቀፍ ብሎም በአለም  ኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ፋዉንዴሽን እዉቅና የሚያገኝ ፕሮግራም ለመመስረት እጅግ በጣም ሰፊ ስራዎች መሰራታቸዉን አዉስተዋል፡፡ የማነቃቂያ ስብሰባዉም በአይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ  በ3 ዓመት ጊዜ ዉስጥ የባችለር ሳይንስ ኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ዲግሪ ስልጠናዉን ለመቅረፅ ከታቀዱ የተለያዩ ተግባራት ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ሶስት መምህራንን ወደ ኩዊንስ ዩኒቨርስቲ ልኮ ኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) በማስተርስ ሳይንስ ዲግሪ እንዲሚያስለጥንም ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡ ይህም ፕግራሙ ከመጀመሩ በፊት የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ተቋማዊ አቅም ይገነባል፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲም በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ዉስጥ ለማጠናቀቅ አራት ዓመት የሚወስደዉን የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) የባችለር ሳይንስ ዲግሪ ፕሮግራም መጀመር ይጠበቅበታል፡፡ እሰከዛ ድረስ ግን የዳሰሳ ጥናት፣ የስርዓተ- ትምህርት ቀረፃ እና ለየኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ፕሮግራም የሚጠቅሙ የሌሎች አገራት ምርጥ ተሞክሮዎች መቅሰም ይከናወናሉ፡፡

የስብሰባዉን መገባደድ ተከትሎ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና የኩዊንሰ ዩኒቨርሲቲ የማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ስኮላርስ ፕሮግራም ቡድኖች በግላቸዉ የተሃድሶ አግልግሎት ለማግኘት አቅም የሌላቸዉ ህፃናትን የሚረዳዉንና በኢትዮጵያ የህፃናት ተሃድሶ ላይ የሚሰራዉን ሺሻየር ሰርቪስስ ኢትዮጵያ የተባለዉን ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጎብኝተዋል፡፡ ድርጅቱ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የነበረ ሲሆን  አሁንም አገልግሎቶቹን እያስፋፋ ይገኛል፡፡ ሺሻየር አምስት የተሃድሶ ክሊኒኮች ያሉት ሲሆን የአገሪቱን ገጠራማ ክፍል የሚያዳረሱ ፕሮግሞች አሉት፡፡ ክሊኒኮቹም በአዲስ አበባ፣ ከአዲስ አባባ እንደወጡ በሚገኘዉ በመናገሻ፣ በድሬዳዋ፣ በሀዋሳ እና በሀረር ይገኛሉ፡፡ በመናገሻ የሚገኘዉ የተሃድሶ ማዕከል የሺሻየር ሰርቪስስ ኢትዮጵያ ትልቁ የተሃድሶ ማዕከል እና መለያ መሆኑን ቀጥሏል፡፡ ቡድኖቹ በተጨማሪም ለባዮሜዲካል የምርምር ተቋምነት የተመሰረተዉን አርማዌር ሀንሰን የምርምር ተቋምን (Armauer Hansen Research Institute) እና ከአጠገቡ የሚገኘዉን የአፍሪካ የሥጋ-ደዌ ተሃድሶ እና ማሰልጠኛ ሆስፒታልን (ALERT Hospital) ጎብኝተዋል፡፡ አለርት በኢትዮጵያ ፊዚዮ ቴራፒ፣ ኦከፔሽናል ቴራፒ እንዲሁም ኦረቶፔዲክ ቴክኖሎጂን በማጣመር የተሃድሶ አገልግሎት በመስጠት አርአያ ነዉ፡፡ ማዕከሉ ለወደፊት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኦከፔሽናል ቴራፒ (የሞያ ህክምና) ተማሪዎች ለተግባር መላማመጃነት ጠቃሚ ይሆናል፡፡