የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማስተርካድ ተማሪዎችን ተቀበለ፡-ለአካል ጉዳተኞች ብሩህ መንገድ ከፈተ

ጥቅምት 2, 2010

በሳሙዔል ማለደ

የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መስከረም 27 እና 28 የማስተርካርድ ስኮላርስ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀበለ፡፡ ቀኑ በአቀባበልና በምዝገባ ጀምሮ ወጣት አዋቂዎቹን ለሰፊዉ የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብና እንደ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ለወደፊት የሚጠብቃቸዉን ጠቅላላ ጉዞ አሰተዋዉቋል፡፡

ሀያዎቹን የማስተርካርድ ሰኮላርስ ተማሪዎች ለመምረጥ የምልመላዉ ሂደት ጥብቅ የነበረ ሲሆን እነዚህን የአካል ጉዳተኛ እና ዉስንነት ያለበቸዉ ወጣቶችን ለመምረጥ የተሄደበትን የሀቀኝነት ጥግ ያሳየ እንደሆነ እሙን ነዉ፡፡ ሲጀምር ማን በእለት ተእለት ኑሮዉ የተጎዳ ነዉ የሚለዉ ቅድሚያ በመስጠት መልማዮቹ ማን ዕድሉ በጣም ያስፈልጋዋል የሚለዉን በእያንዳነዱ አመልካች ቤት ለቤት በመሄድ ያጣሩ መሆኑ ታዉቋል፡፡ በመጨረሻም መልማዩ ቡድን ለአካል ጉዳተኞች፣ የፋይናንስ አጣብቂኝ ያለበቻዉን እና ችላ የተባሉትን የተሻለ እድል መስተቱን አስፈላጊ ሁኖ አግኝተዉታል፡፡

የማስተርካርድ ፋዉንዴሽን እንደ አዉሮፓዊያን አቆጣጠር በ 2006 ተመስርቶ የትምህርት፣ የገንዘብ ማዕቀፍ እና የኑሮ መሠረትን ለማሻሻል እየሰራ ይገኛል፡፡ በትልቋ የአፈሪካ አህጉር ዉስጥ ያለዉ እዉነታ እነደሚያሳየዉ የማስተርካርድ ፋዉንዴሽን በብዛት በብቸኝነት በሚባ መልኩ የሳብ-ሳሃራ አገሮችን እንደሚረዳ ነዉ፡፡ በአፍሪካ ተቀዳሚ አላማዉም የለዉጥ መሪዎችን መፍጠር ነዉ፡፡ በአፍሪካ ቀንድ በቀጣዮቹ አስርት ዓመታት 450 የሚሆኑ የአካል ጉዳት ያለባቸዉ ተማሪዎች የህይወት ዘመን እድል በመስጠት ይህንን አላማዉን ያሳካል፡፡

.

ዶ/ር ሚኪያስ እነዳሉትም ለቀጣዮቹ 7 ዓመታት የተማሪዎቹ ቁጥር በቋሚነት ይጨምራል፡፡ ይህም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ  ክህሎት ያላቸዉን ብዙ ወጣት የአካል ጉዳተኞችን ወደ ፕሮግራሙ እንዲያስገባ ይፈቅድለታል፡፡ ቀጣይነት ያለዉ የቁጥር ጭማሬዉም በፕሮግራሙ የታቀደዉ ኮታ እሰኪሞላ ድረስ ይቀጥላል፡፡

በተጨማሪም እነዚህ የተመረጡት የአካል ጉዳተኛ እና ዉስንነት ያለባቸዉ ወጣት አዋቂዎችን  ጥራት ያለዉ ትምህርትና የድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ክህሎታቸዉን አዉጥተዉ እንዲያሳዩ ይጠበቃሉ፡፡ በአይነቱ በኢትዮጵያ ልዩ በሆነዉ በዚህ ፕሮግራም የአካል ጉዳተኞች የሚያስፈልጓቸዉ ነገሮች በሙሉ ሰለሚሟሉ ለዉጤታማነት እርግጠኛ መሆን ይችላሉ ለዚህም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሩን ለመክፈት ተዘጋጅቷል፡፡

http://www.uog.edu.et/paving-bright-path-disabled-uog-inducts-mastercard-scholars/